
ብርሸለቆ: ጳጉሜን 02/2013 ዓም(አሚኮ) ብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለሀገር ደጀን እና ለወገን አለኝታ የሆኑ ጀግኖችን እያበረከተ ይገኛል።
ትምህርት ቤቱ ዛሬ ለ34ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች ያስመርቃል።
አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን የፈጠረውን ሀገር የማተራመስ ተግባር ለመመከት በርካታ ሀገር ወዳድ ወጣቶች መከላከያን ተቀላቅለው መሠረታዊ የውትድርና ትምህርት እየወሰዱ ነው። የዛሬ ተመራቂዎችም የዚህ አካል ናቸው ተብሏል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሥነ ሥርዓቱን ከቦታው እየተከታተልን እናደርሳለን።
ዘጋቢ፦ ጻዲቁ አላምረው -ከብርሸለቆ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ