
አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ)የ2013 ዓ.ም በጎ ሰው ሽልማት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ የ2013 ዓ.ም በጎ ሰው መንግሥታዊ የሥራ ኀላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ ተሸላሚ ሆነዋል።
ለበጎ ሰው ሽልማት ከ 500 በላይ ሰዎች የተመለመሉ 30 እጩዎች ለሽልማት ታጭተዋል። በ2013 ዓ.ም አስር ዘርፎች ለሽልማት ተመርጠዋል፤ ከነዚህም መካከል በመምህርነት ፣ በሳይንስ ማለትም ህክምና ፣ ቴክኖሎጂ ፣ ምሕንድስና ፣ ኬሚስትሪ ፣አርክቴክቸር፤ በኪነ ጥበብ ፣ በጎ አድራጎት ፣ቢዝነስና ፈጠራ፣ መንግሥታዊ ተቋማት ኀላፊነት ፣ ቅርስና ባህል ፣ ማኅበራዊ ጥናት ፣ ሚዲያና ጋዜጠኝነትና ለሀገሪቱ እድገት በጎ ሥራ ያከናወኑ ዲያስፖራዎች ለዘንድሮ የተመረጡ ዘርፎች ናቸው ተብሏል።
በበጎ ሰው ሽልማት እስከ አሁን ከ170 በላይ ሰዎችን ለሽልማት በቅተዋል፤ ሽልማቱ ዘንድሮ ለ 9ኛ ጊዜ ነው የተከናወነው።
ዘጋቢ፡- ዳንኤል መላኩ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m