
ደሴ፡ ነሐሴ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከወሎ ግንባር አዛዦች መካከል አንዱ የሆኑት ብርጋዴር ጀኔራል ሻምበል ፈረደ አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን እየተመታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አሸባሪ ቡድኑ ከፍተኛ የሰው ኀይል አሰልፎ ወደ ወረባቦና ተሁለደሬ ወረዳዎች ሰርጎ ለመግባት ቢመጣም የጀግናውን የመከላከያ ሠራዊት ጠንካራ ምት መቋቋም አቅቶት ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ነው ቀሪውም እየተመለሰ ነው ብለዋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊቱ ሀገር ለማፍረስ አስቦ የመጣውን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ በከፍተኛ ወኔ እየተፋለመ መሆኑን ገልጸው የሕዝቡ ደጀንነት ከፍተኛ እንደሆነም ብርጋዴር ጀኔራል ሻምበል ፈረደ ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ የቡድኑ አባላት እየተደመሰሱ ነው፤ በቀጣይም በቡድኑ ላይ የሚወሰደው ርምጃ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ተመስገን አሰፋ – ከወሎ ግንባር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m