
ደባርቅ፡ ነሐሴ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን መማክርት የአሸባሪው ትህነግን ወራሪ ቡድን እየደመሰሰ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ የአልባሳትና ሌሎች ቁሳቁስ ድጋፍ አስረክበዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህር መንግሥቱ ሙሉ ሊያጠፋን የመጣን አሸባሪ ቡድን ለማጥፋት ወደኋላ ለማይለው የወገን ጦር ሁሉም የቻለውን ድጋፍ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡
በወቅን የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት አቶ ፋሲካው አንበርብር ወቅን ላይ በነበረው ውጊያ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ ላስመዘገቡት ድል የሕዝቡ ድጋፍ እንዳልተለያቸው ገልጸዋል፡፡
የዳባት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሰውነት ውባለም በዳባት፣ ወቅንና ደባርቅ ዙሪያ በተደረገው ጦርነት የጎንደር ከተማ ባለሀብቶች፣ ነጋዴዎችና ምሁራን ለወገን ጦር በሐሳብ፣ በገንዘብና በቁሳቁስ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው የጸጥታ ኀይሉ በሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን ላይ ለተቀዳጀው ድል የወጣቶች ርብርብ እና የጎንደር ከተማ ሕዝብ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አቶ ሰውነት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን መማክርት በሀገር ውስጥና በኩዬት የሚኖሩ አማራዎችን በማስተባበር ያደረጉት ድጋፍ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን ከምድረ-ገፅ እስከሚጠፋ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለህልውና ዘመቻው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አድኖ ማርቆስ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m