“የወሎ ሕዝብ ለፍቅር እንጅ በእብሪት የተሸነፈበት ታሪክ የለውም” የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰይድ መሐመድ

865

ደሴ፡ ነሐሴ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰይድ መሐመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት “አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ኃይል የወሎን ምድር በውል ባለመገንዘብ ዘሎ ገብቶ እንደ ቡና አርሮ እየተቆላ ነው፤ በመጣበት እግሩም ዘሎ እንዳይመለስ በየመንገዱ እየተቀበረ ነው” ብለዋል።

“ጀግናው የወሎ ሕዝብ፣ ሚሊሻ፣ ወጣቶች፣ ፖሊስ፣ ቆራጥ አመራሮች በየደረጃው ባደረጉት የጀግንነት ተጋድሎ፣ የምንጊዜም ኩራታችን በሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን፣ ልዩ ኀይላችን ታሪክ ሠሪነት አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ኃይል በወሎ ምድር ተሸንፎ ወደ ኋላ በመሸሽ ላይ ይገኛል” ነው ያሉት፡፡

“የወሎ ሕዝብ ለፍቅር እንጅ በእብሪት የተሸነፈበት ታሪክ የለውም” ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው፡፡

ተሸንፎ መውጫ መግቢያ ያጣውን አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ኃይል ጀግናው የወሎ ወጣት፣ ሚሊሻና ሕዝብ በየመንገዱ ከበህ በመማረክና በመደምሰስ የያዙትን የጦር መሳሪያ በመወስድ እንዲታጠቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበስሜን ግንባር አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ ወጣቶች ላደረጉት ፍልሚያና ለከፈሉት የጀግንነት መስዋእትነት መንግሥት ትልቅ ክብር እንዳለው ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ገለጹ።
Next article“የወሎ ወጣቶች የጠላት ትህነግን ወረራ በየአቅጣጫዉ ለመመከት የምታደርጉትን ተጋድሎ በክልሉ መንግሥትና ሕዝብ ስም ምስጋና ሳቀርብላችሁ በታላቅ ኩራት ነው” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር