የዋግ ሕዝብ ከጸጥታ ኀይሉ ጋር በመቀናጀት የተበታተነውን አሸባሪ ቡድን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ነው፡፡

167

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ወራራ የፈጸመው የአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን በብሔረሰብ አስተዳደሩ ወጣቶች እና በፀጥታ አካሉ ቅንጅት ተቀጥቅጦ መደምሰሱን እና የተቀረውም መበታተኑን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከሰሞኑ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

አሁንም የዋግ ሕዝብ ከፀጥታ አካሉ ጋር በመቀናጀት የተበታተነውን የአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን እየለቃቀመ እና አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ታሪክ የማይረሳው ጀብድ እየፈጸመ ነው፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሰቆጣ ከተማ ተዘዋውሮ ባደረገው ምልከታ አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን ሰቆጣ ከተማን ወርሮ በቆየባቸው ቀናት ንጹሃንን ገድሏል፤ በርካቶችን አፈናቅሏል፤ የግለሰቦችን ሀብት እና ንብረት ዘርፏል፤ አውድሟል፤ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ከጥቅም ውጭ አድርጓል፤ መሰረተ ልማቶችን አፈራርሷል፡፡

“ከሕዝብ ጋር ጠብ የለኝም” እያለ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ የሚነዛው የአሸባሪው የትህነግ ቡድን ሰቆጣ ከተማ በወረራ ጊዜ ጤና ጣቢያን ጨምሮ አጠቃላይ ተቋማትን ዘርፏል፤ አውድሟል፡፡ የቴሌኮም፣ የመብራት ኃይል ማስተላለፊያዎች እና መሰል መሰረተ ልማቶችንም ከጥቅም ውጭ አድርጓቸዋል፡፡

ግለሰቦች ገንዘብና ጉልበታቸውን አሟጠው ያፈሩት ሃብት እና ንብረት በአጭር ቀናት በአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን እንዳልነበር ሆኗል፡፡
የአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን ሕፃናት፣ ሴቶች፣ ነፍሰጡር እናቶችንና አዛውንቶችን ሲያሰቃይ እንደነበር ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ አባላት ቤት ለቤት እየዞሩ ምግብ፣ መጠጥ፣ ልብስ እና መሰል ነገሮችን እንዲያቀርቡ ሲያስገድድ እና ሲያንገላታቸው እንደነበር ገልጸዋል፡፡

አሁን የአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻውና የዋግ ሕዝብ አካባቢውን በማጽዳት እና በማረጋጋት ላይ ናቸው፡፡ ከሰቆጣ ከተማና ዙሪያ ወረዳ ተፈናቅለው የነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ይገኛሉ፡፡
ተፈናቃዮች ሃብት ንብታቸው በአሸባሪው ትህነግ ቡድን በመዘረፉ እና በመውደሙ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ከፍያለው ደባሽ- ከሰቆጣ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleሽብርተኛው ትህነግን ከምስረታው እስከ መቃብሩ አፋፍ በጽናት የታገለው “ከፋኝ”
Next articleበስሜን ግንባር አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ ወጣቶች ላደረጉት ፍልሚያና ለከፈሉት የጀግንነት መስዋእትነት መንግሥት ትልቅ ክብር እንዳለው ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ገለጹ።