
በሁሉም የህልውና ዘመቻ ግንባር አካባቢ ላለው ህዝባችን፤ አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በልዩ ኀይል፣ በሚሊሻ፤ ፋኖ እና በመላው ሕዝባችን እየተወሰደበት ባለው ከባድ ምት እና እርምጃ ጠላት እየተበታተነ ይገኛል፡፡
ስለሆነም የሕዝብ ጠላት የሆነው የአሸባሪው እና ወራሪው ትህነግ ቡድን የዘረፈውን የሕዝብ እና የመንግሥት ሃብት ይዞ እንዳይወጣ በየአካባቢው ተደራጅተህ እርምጃ እንድትውሰድ የክልሉ መንግሥት ጥሪ ያቀርባል።
በተለይም በመርሳ ግምባር ሚሌና ጊራና አካባቢ፣ ከመርኮታ ወደ ፋጂ የባቡር መስመሩን ተከትሎ፣ ከጎኃ ጀምሮ ወደ ሚሌ አቅጣጫ፣ በመቄት ግምባር ከገረገራ ጀምሮ እስከ ድልብ ደረስ፣ በላስታ፣ ላሊበላ እና ሙጃ አካባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ጎንደር በማይጠብሪና አካባቢው ጠላት በከፍተኛ ሁኔታ እሸሸ ስለሆነ የጠላት ቡድን አባላትም ሆኑ አንድም የሕዝብ እና የመንግሥት ሃብት ይዞ እንዳይወጣ ሁሉም በአካባቢው እየተደራጀ የሚሸሸው ቡድን ላይ እርምጃ እንዲወስድ እና አስፈላጊን መረጃ ለጸጥታ አካሉ እዲሰጥ የአማራ ክልል መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ነሐሴ 30/2013 ዓ.ም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m