
ባሕር ዳር፡ መስከረም 17/2012 ዓ/ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በሱዳን ካርቱም በሚገኘው ካርቱም ደብረ ሠላም መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓልን አክብረዋል፡፡
በበዓሉ ላይ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች፣ ሠራተኞች፣
የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላትና የኢትዮጵያ ወዳጅ ሱዳናውያን ተገኝተዋል፡፡
በኢፌዴሪ የሱዳን ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አቶ መኮንን ጎሳዬ ለተሳታፊዎቹና ለሃይማኖቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ምንጭ፡- በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ