አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በአረብኛ ቋንቋ ሥርጭት መክፈቱ ተገቢ ውሳኔ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የአልጀዚራ ኀላፊ መሀመድ ተዋከል ገለጹ፡፡

202

አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በአረበኛ ቋንቋ ሥርጭቱን በአዲስ አበባ ስቱዲዮ የማስጀመሪያ መርኃ ግብር አካሂዷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በአማርኛ፣ በአዊኛ በኽምጠኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግረኛ እና በእግሊዘኛ ቋንቋዎች በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ሥርጭቱን ለአድማጭ ተመልካች እያደረሰ ይገኛል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ተናጋሪ ባለው በአረበኛ ቋንቋ ሥርጭቱን ለአድማጭ ተመልካች ለማድረስም ዝግጅቱን ሲያደርግ በመቆየት በአዲስ አበባ ስቱዲዮ የማስጀመሪያ መርኃ ግብር አካሂዷል፡፡

በመርኃግብሩ ላይ በኢትዮጵያ የአልጀዚራ ሚዲያ ኀላፊ መሀመድ ተዋከል እና የህዳሴ ግድብ ተሟጋቹ መሀመድ አል- አሩሲ እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአረብኛ ትምህርት ክፍል መምህራን ተገኝተዋል፡፡

የአማራ ባህልና ወግን እንዲሁም የአብሮነት ኑሮን ለአረቡ ዓለም ለማሳወቅ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የአረብኛ ቋንቋ ሥርጭቱን ለማስጀመር ምክንያት እንደሆነው የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰጠኝ አቡሀይ ተናግረዋል።

ሚዲያው ከአረብኛ ቋንቋ በተጨማሪ በቀጣይም በተለያዩ በኢትዮጽያ ውስጥ ያሉ ቋንቋዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራ ገልጸዋል።

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አረብኛ ቋንቋ መክፈቱ በክልሉ ያሉ የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚ እና ፖለካዊ እንቅስቃሴዎችን ለአረቡ ዓለም ከማድረስ ባሻገር በቋንቋው ለሚግባቡ የሀገሪቱ ዜጎችም አማራጭ መፍጠር መሆኑን የገለጹት ደግሞ በኢትዮጵያ የአልጀዚራ ሚዲያ ኀላፊ መሐመድ ተዋከል ናቸው።

ኮርፖሬሽኑ ሥርጭቱ መጀመሩ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ:- ራሄል ደምሰው – ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየተከዜን ኮሪደር ተገን ያደረገው የጠላት ጦር በአካባቢው የሚሊሻ አባላት ተደመሰሰ፡፡
Next articleከአማራ ክልል መንግሥት የተላለፈ ጥሪ፡፡