
ደባርቅ: ነሐሴ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት በሰጠው መግለጫ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በማይጠብሪ ግንባር በአራት አቅጣጫ ሰብሮ ለመግባት የሞከረው ጠላት በወገን ጦር ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን ገልጿል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን ከትናንት ምሽት ጀምሮ እስከ ዛሬ ቀን ድረስ በማይጠብሪ ግንባር በሚገኙት ግና ሜዳ፣ ዝንጀሮ አፋፍ፣ ወርቅ አዝላ እና በቅሎ ማነቂያ አካባቢዎች በኩል ሰብሮ ለመግባት ሙከራ አድርጎ ነበር ብሏል መከላከያ በመግለጫው፡፡
በአራቱም አቅጣጫ አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በመመታቱ በርካታ ምርኮኛ እና የጦር መሳሪያ መያዙን ነው በግንባር ያለው የመከላከያ ኀይል የገለጸው፡፡
ዘጋቢ፡- ኃይሉ መላክ -ከማይጠብሪ ግንባር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m