በጫት አቅራቢዎች፣ አጓጓዦች፣ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎች፣ አስቃሚዎቾና ተጠቃሚዎች ላይ የጎንደር ከተማ የጸጥታ ምክር ቤት የክልከላ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

340
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን እና የትግራይ ወራሪ ከሌሎች ፅንፈኛ ፀረ ኢትዮጵያ ኀይሎች ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የክልላችን ሕዝብ ህልውናን አደጋ ላይ በመጣል ሕዝባችንን በወረራቸው አካባቢዎች በሙሉ ሁሉንም አይነት ግፎች እየፈፀመ ይገኛል።
ይህ ኃይል ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማፈራረስ ካለው ህልም ባሻገር ከአማራ ሕዝብ ላይ የማወራርደው ሒሳብ አለኝ በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ መነሻ በማድረግ ወረራ በፈፀመባቸው የክልሉ አካባቢዎች በሕዝቡ ላይ የበቀል በትሩን ማሳረፍ ጀምሯል።
ይህን በማገናዘብ ወረራውን ሊመክት የሚችል የአካባቢውን ሰላም እና ደኅንነት አስተማማኝ እንዲሆን የሚያደርግ መንፈሰ ጠንካራ ወጣት ኀይል በሥነ ልቦና የተገነባ ትውልድ ደግሞ ሀገርን ከጥቃት እና ከወረራ እንዲሁም ከጥፋት መታደግ የሚቻለው ከሱስ የፀዳ በሥነ ምግባር የታነፀ በመሆኑ ይህንን ትውልድ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት መነሻ በማድረግ የጎንደር ከተማ የጸጥታ ምክር ቤት በጫት አቅራቢዎች አጓጓዦች፣ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎች፣ አስቃሚዎችና ተጠቃሚዎች ላይ የክልከላ ውሳኔዎችን አስተላልፏል ።
በመሆኑም ከነሐሴ 28/2013 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ ጫት ከሌላ አካባቢ ማጓጓዝ፣ መቸርቸር፣ ማከፋፈል፣ ማስቃምና መቃም ተከልክሏል።
በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ምክር ቤቱ ክልከላ ባደረገባቸው ተግባራት ላይ ሲሳተፍ የሚገኝ ተሽከርካሪ ግለሰብም ሆነ ድርጅት በሐረግ የሚጠየቅ መሆኑን ምክር ቤቱ በአክብሮት ይገልጻል።
ይህንን የከተማዋ የጸጥታ ኀይል ተከታትሎ እንዲያስፈፀም ታዟል።
በጫት ንግድ የተሰማራችሁ የከተማችን የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘርፍ ቀይራችሁ በሌሎች የንግድ የአገልግሎት እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ለመሰማራት ባቋቋምነው ግብረ ኀይል አማካኝነት አስፈላጊውን ጥረት እና እገዛ የሚደረግ መሆኑን እናሳስባለን።
የጎንደር ከተማ ኮምዩኒኬሽን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር በአርቲስት ዓለማየሁ እሸቴ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።
Next article“አሸባሪው የትህነግ ቡድን ዓላማው አሸንፎ ሀገር መምራት ሳይሆን እንደ ሀገር ኢትዮጵያን፣ እንደ ሕዝብ አማራን አንገት ማስደፋት ነው” ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር