የወገን ጦር አሸባሪውን ትህነግ ከሰቆጣ አስለቅቋል፡፡

540

ሰቆጣ፡ ነሐሴ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል እና የዋግ ሚሊሻ እና ወጣቶች ሰሞኑን ባደረጉት ዘመቻ ዛሬ ረፋድ ሦሰት ስዓት አካባቢ ሰቆጣ ከተማና አካባቢውን ከአሸባሪው ትህነግ አስለቅቋል፡፡

በዘመቻው የወገን ጦር ወራሪውን የትህነግ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ቀጥቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የማጽዳት እና የአሰሳ ሥራ እየሠራ መኾኑን አሚኮ ሰቆጣ በመገኘት ተመልክቷል፡፡

የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ ለልዩ ኃይሉ እና ሚሊሻው ደማቅ አቀባበል አድርገዋል፡፡

አሚኮ ያነጋገራቸው ወጣቶች የዋግ ሚሊሻ እና ወጣቶች ዘመቻው እንዲሳካ ያደረጉት ተጋድሎ ለድል ማብቃቱን እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

ድሉ የመላው ሀገሪቱ እስከሚሆን ድረስ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡

ዘጋቢ:- ንጉሡ ማሩ – ከሰቆጣ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleለወገን መኖርን በተግባር የኖሩ…
Next articleእኒህ ወራሪዎች የጠፋቸው ቅጡ፣ እንጀራ ልመና ክላሽ ታጥቀው መጡ፣ ቀኑ ወልቃይት ነው ተከዜ ወራቱ፣ መቁጠሪያው ጎንደር ነው ዓመተ ምህረቱ።