ለወገን መኖርን በተግባር የኖሩ…

204

ኮምቦልቻ፡ ነሐሴ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አቶ ሰይድ ጉማቴ እና ባለቤታቸው ወይዘሮ ሰዓዳ ይባላሉ፡፡
ነዋሪነታቸው በኮምቦልቻ ከተማ ነው፡፡ አሸባሪው ትህነግ በአማራ ክልል በፈፀመው ወረራ አካባቢያቸውን ለቀው ኮምቦልቻ ከተማ የደረሱ 106 ተፈናቃዮችን በማስጠለል የወገን አለኝታነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ከሰሜን ወሎ ዞን አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን ካስጠለሉት ከአቶ ሰይድ ጉማቴ ጋር አሚኮ በነበረው ቆይታ ለወገኖቻችን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት መድረስና አለናችሁ ልንላቸው ይገባል፤ እነሱ ጊዜያዊ ችግር ላይ ወድቀው እንጂ አስበውበት ከቤታቸው ስላልወጡ የእኛን እገዛ ይፈልጋሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ያለን ቤት ሁሉንም ለማስተናገድ በቂ ባይሆንም በምንችለው አቅም 57 ያክሉን በቤቴ ሌሎቹን 49 የሚሆኑትን ደግሞ ቤት ተከራይቼ እየኖሩ ይገኛሉ” ብለዋል፡፡ ይህም ችግሩ መፍትሔ እስከሚያገኝ እገዛቸው እንደማይለይ ነው አቶ ሰይድ የተናገሩት፡፡

ባለቤታቸው ወይዘሮ ሰዓዳ በበኩላቸው ከተፈናቃዮች መካከል ሦስት ነፍሰጡሮች ስለሚገኙ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ክትትል እንዲጀምሩ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ “ወገኖቻችን ዛሬ ለስቃይ ቢዳረጉም ነገ ወደ ቤታቸው መመለሳቸው አይቀርምና ከወገኖቻችን ጋር ያለንን ተካፍለን እንኖራለን፣ ልጆቻቸውንም ከልጆቼ ጋር እኩል እናኖራቸዋለን” ነው ያሉት፡፡

በአቶ ሰይድና ባለቤታቸው ወይዘሮ ሰዓዳ ቤት ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮችም ለተደረገላቸው እገዛና የወገን ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ተመስገን አሰፋ – ከኮምቦልቻ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበሰሜን ጎንደር ዞን የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን ድባቅ እየተመታ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳደሪ ያለዓለም ፈንታሁን ገለጹ፡፡
Next articleየወገን ጦር አሸባሪውን ትህነግ ከሰቆጣ አስለቅቋል፡፡