ዞኖች ጋር በመቀናጀት የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድንን እየደመሰሱ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ገለጸ።

199

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 26/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ጠሉና ሀገር የማፍረስ ዓላማን አንግቦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሽብርተኛው ትህነግ በተለያዩ አካባቢዎች ጥፋት እየፈጸመ ይገኛል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ እንዳሉት ዞኑ ከአጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች ጋር የጠበቀ አደረጃጀት በመፍጠር ወራሪውን እና ሽብርተኛው ትህነግን የመደምሰስ ሥራ እየተሠራ ነው። ከመደበኛ ጸጥታ ኀይሉ በተጨማሪ ወጣቶች ተደራጅተው ግንባር ድረስ በመዝመት ሀገርን ለመታደግ የሽብርተኛው ትህነግ ቡድንን እየተፋለሙ ነው ብለዋል።

የሽብርተኞቹን ኦነግ ሸኔና ትህነግ ሴራ ለማክሸፍ ከአጎራባች ዞኖች ጋር እየሠሩ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

አቶ ሰይፉ ወርቄ ሰዶማ እና ድሬ ሮቃ በተባሉ ቀበሌዎች ነዋሪዎች የፈጸሙትን ጀብድ የደቡብ ወሎ ሕዝብም ይደግመዋል ብለዋል፡፡

አሸባሪው ትህነግን ከመደምሰስ ጎን ለጎን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አቶ ሰይፉ ገልጸዋል፡፡ ለሕልውና ዘመቻውም ሁሉን አቀፍ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደቀጠለም ጠቅሰዋል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ለህልውና ዘመቻው ከሕዝቡ 95 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንም ምክትል አስተዳዳሪው አስታውቀዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተባበረ ክንድ የሽብርተኛው ትህነግን እድሜ ለማሳጠር በትጋት እንዲሠራ ምክትል አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ፡- ሰለሞን አንዳርጌ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየማይካድራ ንጹኃን በግፍ የጨፈጨፈውን አሸባሪ ቡድን ለመቅበር በሕብረት እየሠሩ መሆኑን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራና የምዕራብ ጎንደር ዞኖች አስታወቁ።
Next articleሽንፋን በአራት አቅጣጫ ከቦ ጦርነት የከፈተው የጠላት ጦር እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑ ተገለጸ፡፡