
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ወይዘሮ ዘምዘም አሊ ነዋሪነታቸው በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ነው።
አሸባሪው የትህነግ ቡድን በፈጸመው ወረራ ሰዎችን ገድሏል፤ ንብረት አውድሟል ነው ያሉት።
በሽብር ቡድኑ ወረራ ምክንያት ጃራ በተባለ ቦታ ለመጠለል እንደተገደዱም ነግረውናል።
ወይዘሮ ዘምዘም የመጀመሪያ ልጃቸውን በጃራ አካባቢ በእናታቸው አዋላጅነት ተገላግለዋል።
አሚኮ ወደ ስፍራው ባቀናበት ወቅት ወይዘሮ ዘምዘም ከወለዱ ሁለተኛ ቀናቸው እንደሆነና እንኳን ለአራስ የሚያስፈልጉ ነገሮች ቀርቶ ምግብ፣ ልጃቸውን የሚያስተኙበት ፍራሽ እና የሚጠጣ ውኃ ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
“ከወለድኩ ሁለት ቀኔ ነው፤ አሸባሪው ትህነግ በቀያችን ጥቃት በመክፈቱ ለመሰደድ ተገድጃለሁ” ብለዋል።
ተፈናቃዮችን ለማየት ወደ ሥፍራው ያቀኑት ዶክተር ሞገስ በርየ ከተፈናቃዮች መካከል የወለዱ እና የመውለጃ ጊዜያቸው የተቃረቡ በርካታ እናቶች መኖራቸውን ገልጸዋል። አልሚ ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ለማድረስ እየተሠራ እንደሆነ አስረድተዋል።
ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግም ተጠይቋል።
ዘጋቢ፡- ከድር አሊ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m