
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከቱርክ አምባሳደር ኢርፋን ናዚር ኦግሉ ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም ሁለቱ አምባሳደሮች በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል ያለውን ጠንካራ ወዳጅነት እና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት በተመለከተ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
በተጨማሪም፣ አምባሳደር ይበልጣል በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ያለውን የድንበር ሁኔታ እንዲሁም የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ስላለው አሁናዊ ሁኔታ ማብራሪያ መስጠታቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m