
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ህወሓት የአሜሪካ ተራድኦ ደርጅት መጋዘኖችን እንደዘረፈ በኢትዮጵያ የድርጅቱ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ተናገሩ፡፡
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ህወሓት ሁኔታውን ያለአግባብ እየተጠቀመበት እንደሆነ እናምናለን ብለዋል፡፡
ከተረጂዎች ላይ እርዳታን በኀይል እየነጠቀ እንደሆነ ይሰማናል ያሉት ዳይሬክተሩ እርግጠኛ ሆነን መናገር የምንችለው ግን የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላት ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ ያሉትን የእርዳታ መጋዘኖቻችንን ዘርፈዋል፤ ይህ የምናውቀው ሀቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አሁን በግልጽ የምናውቀው ነገር የህወሓት ወታደሮች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖችን ዘርፈዋል፣ መኪኖችን ሰርቀዋል በየመንደሮቹ ብዙ ውድመትን አድርሰዋል ያሉት ዳይሬክተሩ ይህ ለተጎጂዎቹም ሆነ ለእኛ ለረጂዎቹ እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንቀሳቀሰው ሀገሪቱ አሁን ችግር ላይ ስላለች አይደለም ብለዋል፡፡
ይልቁንም ኢትዮጵያ ዓለም ላይ ካሉ ምርጥ አጋሮቻችን መካከል አንዷ ነች ያሉት ዳይሬክተሩ ከኢትዮጵያ ጋር ስላለን አጋርነት በእጅጉ እንጨነቃን ነው ያሉት፡፡
አንዳንድ ጊዜ ኅብረተሰቡ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኅን የሚሰራጩትን ያልተረጋገጡ ወሬዎች በመያዝ የኢትዮ አሜሪካ ግንኙነት እንደሻከረ ያስባሉ ያሉት ዳይሬክተሩ ነገር ግን እንደአሁኑ ከኢትዮጵያ ጋር ተባብረን የሰራንበት ጊዜ የለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ኢብኮ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m