
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ ባለሃብት አቶ አሕመድ ኑሩ ለሕዝብ ሲሉ መስዋእትነት ለከፈሉ ጀግኖች ክብር ይገባቸዋል፤ ታሪክም ሲዘክራቸው ይኖራል ብለዋል።
የጀግኖችን ቤተሰብ ማገዝ ከሁሉም የአማራ ሕዝብ የሚጠበቅ ተግባር ነው ያሉት ባለሃብቱ አቶ አሕመድ በጎንደር ከተማ ለሚኖሩ የሕይወት መስዋእትነት ለከፈሉ የጀግኖች ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው የ140 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።
አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡ የጀግኖች ቤተሰብ አባላት አርበኛ ገበየሁ እንየው “ወንድሜ ለሕዝብ ክብር ሲል ቢሰዋም ለቤተሰቡ እየተደረገ ያለው ድጋፍ የሚያበረታታ ነው” ብሏል።
ሌላኛዋ ድጋፍ የተደረገላቸው ወይዘሮ ሰርካለም ቦጋለ “ባለቤቴ ሕዝብን በማስቀደም ቢሰዋም እንደ አቶ አሕመድ ኑሩ አይነት ግለሰቦች አይዟችሁ እያሉን ነው፤ ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል” ብለዋል።
ጀግኖቹ የተሰውለት የሕዝብ ክብር እንዲጠበቅ ሁሉም ኀላፊነቱን በመወጣት የሕልውና ዘመቻውን መቀላቀል አለበት ነው ያሉት።
ዘጋቢ፡- ጳውሎስ አየለ-ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m