“ሽብርተኛው ትህነግ ደሴ ከተማ ገብቶ እንዲዘርፍ እና የአማራነት ክብራችንን እንዲነካ አንፈቅድም” የደሴ ከተማ አስተዳደር ነጋዴዎች

546

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ለህልውና ዘመቻው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ወደ ግንባር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን የደሴ ከተማ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ተናግረዋል፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡ የትህነግ ወራሪ እና አሸባሪ ቡድን የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት እና ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየጣረ ይገኛል፡፡ ቡድኑ በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎችም በሕዝብ እና በመንግሥት ንብረት ላይ ዘረፋና ውድመት ፈጽሟል፡፡

ቡድኑ ወደ ደቡብ ወሎ ሰርጎ ለመግባት እየጣረ መሆኑን የደሴ ከተማ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት አንስተዋል፡፡ ይህንን ወራሪ እና አሸባሪ ቡድን ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡

”የሽብር ቡድኑ አማራን ለማጥፋት እና ኢኮኖሚውን ለማዳከም እየጣረ በመሆኑ ወደ ደሴ ከተማ ገብቶ እንዲዘርፍ እና የአማራነት ክብራችንን እንዲነካ አንፈቅድም” ብለዋል፡፡

የሽብርተኛው ትህነግን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ በማክሸፍ ሁሉም አካባቢውን ከዘረፋና ከውድመት፣ ሴቶችን ከመደፈር ማዳን ግድ እንደሚል ነው በውይይቱ የተነሳው፡፡

የከተማዋ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት የሀገር መከላከያ ሠራዊቱን፣ ልዩ ኀይሉን፣ ሚሊሻውን እና ፋኖውን በገንዘብ እና በቁሳቁስ ከመደገፍ ባሻገር ግንባር ድረስ ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አበበ ገብረ መስቀል የትህነግ ወራሪ ቡድን የወሎ ምድር መቀበሪያው እንዲሆን የንግዱ ማኅበረሰብ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አድንቀዋል፡፡

ሽብርተኛው ትህነግ ንብረት እንዲዘርፍ፣ እንዲያወድም እና የሕዝቡን ክብር ዝቅ እንዲያደርግ መፍቀድ እንደማይገባ እና ሁሉም በነቂስ ወጥቶ እንዲፋለመው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡-አሊ ይመር-ከደሴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበማይጠብሪ ግንባር በደባርቅ ወረዳ በጫንቅና በዳባት ወረዳ ጭና ቆርጦ ለመግባት የሞከረው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ተደመሰሰ።
Next articleባለሃብቱ ለሕዝብ ክብር ሲሉ በተለያዬ ግንባር የሕይወት መስዋእትነት ለከፈሉ ለጀግኖች የቤተሰብ አባላት የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።