
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ ጥዋት በደባርቅ ከተማ በጫንቅና በዳባት ወረዳ ጭና ቆርጦ ለመግባት የሞከረው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በመከላከያ ሠራዊት፣ በልዩ ኃይል፣ በሚሊሻና ፋኖ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት የዳባት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሰውነት ውባለም ለአሚኮ ገልጸዋል።
ወራሪው ቡድን ያሰበው እንዳልተሳካለት ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት ሕዝቡን በማንቃት የተሠራው ሥራም ውጤት አስመዝግቧል ነው ያሉት።
የገባበት አካባቢም እሾህ ሆኖ ጠብቆታል ብለዋል፤ አጅሬ ጃኖራን ቆርጦ ለመሄድ ቢያስብም ተደምስሶ መቅረቱን ተናግረዋል።
ዓላማው በአካባቢ ሽብር ፈጥሮ ከግብፅ ተላላኪዎች ለመገናኘት ነበር፤ የጸጥታው ኀይል ከአራት ቀን በላይ ውጊያ አድርጓል፤ በተሠራው ጠንካራ ሥራም ማለፍ አልቻለም ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው። ቆርጦ በመግባት ደባርቅንና ዳባትን ለማለያየት ያሰበው ዓላማም ከሽፏል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው- ከማይጠብሪ ግንባር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m