
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) እኛ የታሪክ ሠሪ ልጆች ነን ያሉት የአንባሰል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ጌታቸው ጽጌ አሸባሪው የትህነግ ቡድን በውሸት ተጸንሶ በክህደት ያደገ ከነውሸቱ ለመቀበር በመንፈራገጥ ላይ ያለ አጥፊ ቡድን ነው ብለዋል፡፡
አቶ ጌታቸው ኢትዮጵያዊያን በእሴቶቻቸው የሚኮሩ፣ በታማኝነታቸው እና በሀገር ወዳድነታቸው ቀና ብለው በመራመድ ዘመናትን የተሻገሩ፣ ለክብራቸው የሚዋደቁ የዚያ ዘመን ታሪክ ሰሪ ልጆች ናቸው ነው ያሉት።
ዳሩ ግን በዚች ቅድስት ሀገር ላይ ፈተናዎች ይበዙባት እንደነበርና በቁርጥ ቀን ልጆቿ ክብሯን ሳታስደፍር የኖረች ሀገር መሆኗን የተናገሩት አቶ ጌታቸው፣ ወርቅን እሳት ያጠራዋል እንጅ አያጠለሸውም እንዲሉ ይበልጥ አንድነቷን አስጠብቃ የኖረች ሀገር ስለመሆኗ የኋላ ታሪኳ ምስክር እንደሆነ ነው ያብራሩት።
አቶ ጌታቸው እንደ ሰው በላው ቡድን ውሸት ሳይሆን የአንባሰል ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪውን ለመቅበር የተዘጋጅ ናቸው ብለዋል።
የአንባሰል ከተማ ሰላም መሆንን በቦታው ተገኝቶ ያረጋገጠው የጋዜጠኞች ቡድን ማኅበረሰቡ ከየእለት ተግባሩ ጎን ለጎን ጠላትን ለመፋለም ያላቸውን ቁርጠኝነት ማረጋገጥ ችሏል።
አቶ ጌታቸው እንደነገሩን ውጫሌና አካባቢዋ ለእንግዶች ምቹ ለጠላቶች ግን ረመጥ ናት። ከአጼ ሚኒሊክ ጋር ታሪክ የምትጋራዋ ከተማ እና ሕዝቦቿ የዋዛ አይደሉምና አሸባሪውን ቡድን እንዳመጣጡ ይሸኙታልም ብለዋል። አስተዳዳሪው ሁሉም አካል የዚህን አረመኔ ቡድን ተግባር በመረዳት ሊረባረብ ይገባል፤ ጨዋታውም ከጊዜ ጋር መሆን አለበት ነው ያሉት።
ዘጋቢ፡- ሰለሞን አንዳርጌ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m