አሸባሪው እና ወራሪው የትህነግ ቡድን ከእያንዳንዱ የቤተሰብ አባላት ወደ ጦርነት በግዴታ እንዲገቡ እያደረገ እንደሚገኝ በማይጠብሪ ግንባር እጃቸውን የሰጡ የቡድኑ አባላት ገለጹ፡፡

328

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 23/2013 ዓ.ም (አሚኮ)እጃቸውን ከሰጡት የአሸባሪው እና ወራሪው የትህነግ ቡድን አባላት ውስጥ ጎይቶም ሀዱሽ አንዱ ነው፡፡ የእንዳባጉና ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ አሸባሪው የትህነግ ቡድን ባደራጃቸው ካድሬዎች ከሰፈር ታፍሶ ወደ ጦርነት እንደተማገደ ነው የገለጸው፡፡ ጎይቶም አሸባሪው ትህነግ ባመጣው መዘዝ የትግራይ ሕዝብ በርሃብ የሚጠበሰው አንሶት ከወንድም ሕዝብ ጋር እንዲጋጭ በግድ ወደ ጦርነት እየተማገደ ነው ብሏል፡፡

አሸባሪው እና ወራሪው የትህነግ ቡድን ከእያንዳንዱ ቤተሰብ ቢያንስ ሁለት የቤተሰብ አባላት ወደ ጦርነት በግዴታ እንዲገቡ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ወረራ ፈጽመው እንዲዘርፉ፣ እንዲገድሉ እና እንዲያሸብሩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው እንደመጡም ጎይቶም አስታውቋል፡፡ ይህንን ላለመፈጸም ሲል በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው የጸጥታ ኀይል እጅ መስጠቱን ነው ጎይቶም የተናገረው፡፡

ሌኛው የሽብር ቡድኑ አባል ወጣት ግርማዬ ቴዎድሮስ ከትግራይ ክልል የአዲአሮ አካባቢ ነው ተገዶ ወደ ጦርነት የተላከው፡፡ ግርማዬ የትግራይ ሕዝብ ሽብርተኛው ትህነግ እያለ ምንም በሰላም መኖር እንዳልቻለ ነው በምሬት የገለጸው፡፡ የእርሻ ሥራቸውን በአግባቡ ማከናወን ባለመቻሉ ሕዝቡ ለርሃብ እየተጋለጠ መሆኑን ተናግሯል፡፡

አሸባሪውና ወራሪ ቡድኑ የእርዳታ እህል እንኳን እንዳይደርስ እያስተጓጎለ ነው ብሏል፡፡በዚህም ሕዝቡ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን ገልጿል፡፡ አማራ እና አፋር ክልል ሄዳችሁ ዘርፋችሁ ብሉ ተብለው እንደሚላኩ ነው ቴዎድሮስ የተናገረው፡፡ በአሸባሪው ትህነግ ቡድን ውስጥ የሚገኝ የትግራይ ወጣት የቡድኑ እኩይ ድርጊት ፈጻሚ ላለመሆን ለጸጥታ ኀይል በሰላም እጁን እንዲሰጥ ቴዎድሮስ ጠይቋል፡፡

ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው-ከማይጠብሪ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከምድረገጽ እስኪጠፋ ትግላቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በወልቃይት ጠገዴ የከፋኝ መሥራች አባላት ገለጹ።
Next articleወራሪው እና አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሀራ ገበያ ከተማ አስተዳደር ያደረሰው ጥፋት ለሕዝብ ያለውን ጥላቻ እንደሚያሳይ የከተማዋ ከንቲባ ገለጹ፡፡