“ዩኒቨርሲቲው በአዲስና በዘመናዊ አስተሳሰብ ተቃኝቶ እየሠራ ነው” የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

106
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የመቅዳላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላፉት የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ታምሬ ዘውዴ (ዶክተር) ለተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የተሰጣቸውን ትምህርት በስኬት አጠናቀው ለምረቃ በመብቃታቸው እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡
የአንድን ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት ትምህርት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡
መንግሥት የከፍተኛ ተቋማትን በማስፋፋትና በማሻሻል ከፍተኛ ሥራ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ አዳዲስ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መስፋፋታቸው የኅብረተሰቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ መንግሥት እየሠራ መሆኑን የሚያሳይ ነውም ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ዩኒቨርሲቲው በአዲስና በዘመናዊ አስተሳሰብ ተቃኝቶ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ሰባት የምርምር ጣቢያዎችን በማመቻቸት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምርምር እያካሄደ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር አቅሙና በሰው ኃይል በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡
ተማሪዎች መንግሥትና ሕዝብ የጣለባቸውን ኀላፊነት ለመወጣት የሚያበቃ መሠረታዊ ትጥቅ መታጠቃቸውንም አብራርተዋል፡፡
ያገኙት ዕውቀት ወደ ሥራ ዓለም መግቢያ በር እንጂ መጨረሻ አለመሆኑን ተገንዝበው በንባብ እና በተጨማሪ ትምህርት ራሳቸውን በማብቃት ሀገርና ሕዝብን እንዲያለግሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ልጄን ወደ ሌላ የሕክምና መስጫ ተቋም የምወስድበት አቅም የለኝም” ልጃቸው የታመመባቸው እናት
Next articleትግላችን ፍትሐዊ ነውና ኢትዮጵያ ማሸነፏን ትቀጥላለች!