“ልጄን ወደ ሌላ የሕክምና መስጫ ተቋም የምወስድበት አቅም የለኝም” ልጃቸው የታመመባቸው እናት

147
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን በፋርጣ ወረዳ የጋሳይ ጤና ጣቢያን ከዘረፈና ካወደመ በኋላ የአካባቢው ነዋሪዎች ለከፍተኛ እንግልት፣ ሕመምና ሞት ተጋልጠዋል።
የአሚኮ የጋዜጠኞች ቡድንም የጤና ጣቢያውን ውድመትና ዘረፋ ተመልክቷል። ወራሪው ቡድን የሚጠቅመውን ቁሳቁስ ዘርፎ በመውሰድ ያልተመቸውን ደግሞ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” እንዲሉ ሙሉ በሙሉ አውድሟል።
ወይዘሮ ፋንታነሽ ደጀን ከእስቴ ወረዳ ከገዳያት ቀበሌ ሕፃን ልጃቸው ታሞባቸው ወደ ፋርጣ ወረዳ ጋሳይ ጤና ጣቢያ መምጣታቸውን ተናግረዋል። ልጃቸውን ለማሳከም ከሦስት ቀናት በፊት እዚሁ ጤና ጣቢያ ቢገኙም ጤና ጣቢያው በመውደሙ አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም።
ጤና ጣቢያው መውደሙ መረጃው የሌላቸው ወይዘሮዋ ልጃቸው በጠና ስለታመመባቸው የ4 ሰዓት የእግር ጉዞ በመጓዝ ወደ ጤና ጣቢያው ቢመጡም አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ ሲያውቁ ልባቸው በሀዘን ተሰብሯል። የልጃቸው በጠና መታመምምና አገልግሎቱን አለማግኘታቸውም አሳስቧቸዋል።
ወይዘሮ አዲና ጥጋብም ከጉና በጌ ምድር ወረዳ ከአጣ ሲፋጥራ ቀበሌ ነው ልጃቸውን ለማሳከም ወደ ጋሳይ ጤና ጣቢያ የመጡት። በዚህ ክረምት ወቅት የዝናብና ጭቃ እንግልትን ተቋቁመው የ2 ሰዓት የእግር ጉዞ ተጉዘው ቢመጡም አገልግሎቱን ማግኘት አልቻሉም። ወደ ሌላ አካባቢ ልጃቸውን በመውሰድ ለማሳከም አቅም እንደሌላቸውም ወይዘሮ አዲና ተናግረዋል።
ወይዘሮ አዲና የልጃቸውን እጣ ፋንታም አሳስቧቸዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ- ከጋሳይ ከተማ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሕጻናትን እና ነፍሠ ጡር እናቶችን ለጦርነት ማሠለፉ ሕዝባዊ ጦርነት ስለመክፈቱ ማረጋገጫ እንደሆነ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
Next article“ዩኒቨርሲቲው በአዲስና በዘመናዊ አስተሳሰብ ተቃኝቶ እየሠራ ነው” የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት