
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አርቲስት ተሾመ በላይ (ተሾመ ባለሀገሩ) በወሎ ግንባር ሀገራቸውን ከአሸባሪ ቡድኑ ለመጠበቅ እየተዋደቁ ያሉትን የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ፣ ፋኖ እና ሌሎች የጸጥታ አካላትን ግንባር በመገኘት አበረታቷል፡፡
አርቲስቱ እንዳለው ኢትዮጵያ እንኳን ዛሬ በጣሊያን ወረራ ወቅትም በጦር በጎራዴ ለጠላት አልተንበረከከችም፡፡ አባቶች በአንድነት ቆመው ጠላትን አሳፍረው እንዳሸነፉት ሁሉ “እኛም የአባቶቻችንን ታሪክ በመድገም የኢትዮጵያን ጠላቶች የመቅበር ሥራ በጋራ መሥራት አለብን” ብሏል፡፡
ኢትዮጵያዊነት ጀግንነት ነው “የወታደር ልጅ ነኝ ኢትዮጵያ ስትደፈር ቆሜ አላይም” ነው ያለው፡፡ አርቲስት ተሾመ በላይ (ተሾመ ባለሀገሩ) አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግብዓተ መሬቱን ለማፋጠን ሁሉም ኢትዮጵያውያን በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ዘጋቢ፡- ተመስገን አሰፋ-ከወሎ ግንባር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ