የኢትዮጵያን ሕልውና በዘላቂነት ለማረጋገጥ አሸባሪው ትህነግ ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ገለጹ፡፡

2274
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አርበኛ መሳፍንት ወራሪው እና ሽብርተኛው ትህነግ የንጹሃንን ሕይወት እየቀጠፈ ነው፤ የግልና የመንግሥት ንብረት እየዘረፈ ነው፤ የላልይበላ፣ የዋልድባ እና ሌሎች ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶችን እያወደመ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ ሀገር አፍራሽ ነቀርሳ በገባበት ሁሉ ሊቀበር ይገባል ብለዋል አርበኛ መሳፍንት።
አርበኛው ፋኖ የአማራውን ብሎም የኢትዮጵያን ህልውና፣ ታሪካዊ ቅርሶችን እና የባንዲራዋን ክብር ለመጠበቅ ሽብርተኛው ትህነግን ለመደምሰስ በቆራጥነት በሁሉም ግንባሮች እየተፋለመ እንደሚገኝ አርበኛ መሳፍንት ገልጸዋል።
አሸባሪው ትህነግ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ አንጂ ሀገርን የማፍረስ አቅም እንደሌለውም ገልጸዋል። ሁሉም በጋራ በመቆም ይህንን የሽብር ቡድን ከምድረ ገጽ ማጥፋት እና የሀገርን ሰላም ብሎም ህልውና ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡
“አሸባሪው ትህነግ የጭካኔ በትሩን በንጹሃን ላይ ሊያሳርፍ አይገባም፤ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ እንዲጥል አንፈቅድም፤ በመጣበት እንዲመለስ ሳይሆን በመጣበት ነው የምንቀብረው” ብለዋል አርበኛ መሳፍንት፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ ጠላት የሆነውን ሽብርተኛ የትግራይ ወራሪ ኀይል ለማጥፋት በሚደረገው ርብርብ ከፀጥታ አካላት ጎን ሊሰለፍ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ሽብርተኛው ትህነግ የንጹሃንን ሕይወት እየቀጠፈ፣ ንብረት እየዘረፈ እና እያወደመ ነው፤ ሁሉም ይህንን የሽብር ቡድን እስከወዲያኛው ለመቅበር መፋለም እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው-ከማይጠብሪ ግንባር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ተልኮ የተሰጣቸው ተጠርጣሪዎች በደሴ ከተማ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡
Next article42 የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ እና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ቡድን አባላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡