
ባሕር ዳር፡ መስከረም 17/2012 ዓ/ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የጂግጂጋ ቅርኝጫፍ ጽሕፈት ቤት የቶጎ ጫሌ መቅረጫ ጣቢያ በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ 12 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መያዙ ተነግሯል፡፡
በፍተሻ እጅ ከፍንጅ እንደተያዘ የተገለጸው ግለሰብ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ የሚያገኘውን ብር የሚያከማችበት የሦስት የተለያዩ ባንኮች ደብተሮች እንደተገኙበትም የገቢዎች ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡