በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ ነፋስ መውጫ ከተማ የዩኤስ አይ ዲ ቅርንጫፍ የሆነው ኤፍ-ኤች ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን መዘረፉ ተገለጸ፡፡

742
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ ነፋስ መውጫ ከተማ የሚገኘው የዩኤስ አይ ዲ ቅርንጫፍ የሆነው ኤፍ-ኤች ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ንብረቶች ውድመት እና ዘረፋ እንደተፈጸመባቸው የድርጅቱ ኀላፊ ተናግረዋል፡፡
የኤፍ-ኤች ኢትዮጵያ የላይ ጋይንት ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አንተነህ አዳሙ እንዳሉት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የሠራተኞች መኖሪያ ቤትን ጨምሮ፣ የእህል መጋዘኖች፣ በርካታ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች እና ጋራዥም ሙሉ በሙሉ ወድሟል ነው ያሉት።
መኪናን ጨምሮ 25 የፕሮጀክቱ የሞተር ሳይክሎች በወራሪው ቡድን መዘረፋቸውን ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
አቶ አንተነህ ለአደጋ ጊዜና ለሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውል 4 ሺህ 551 ኩንታል በላይ እህል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን መወሰዱንም አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ-ከነፋስ መውጫ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“አሸባሪው ህወሃት ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ልብና ህሊና ውስጥ ወጥቷል” አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ
Next articleከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ተልኮ የተሰጣቸው ተጠርጣሪዎች በደሴ ከተማ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፡፡