
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 20/2013 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ በጥሩ ብርሃን መሠረታዊ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ያሰለጠናቸውን ምልምል የልዩ ኀይል አባላት አስመርቋል።
በምረቃው ያነጋገርናቸው ሰልጣኞች እንዳሉት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ላይ እያደረሠ ያለውን ጉዳት ለመቀልበስ ወደ ክልሉ ልዩ ኀይል ተቀላቅለዋል። በዚህም ባገኙት የተግባር እና ንድፈ ሐሳብ ስልጠና ታግዘው በግንባር ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አሸባሪው ቡድን ከፋፋይ እና ጸረ አንድነት ኀይል በመሆኑ እስከመጨረሻው መታገል እንደሚገባ ነው የተናገሩት።
“አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን እንቀብረዋለን” ብለዋል የልዩ ኀይል አባላቱ፡፡
ያለ መስዋእትነት ድል መጎናጸፍ እንደማይቻል የገለጹት ተመራቂ የልዩ ኀይል አባላቱ ወጣቱ ልዩ ኀይል እና መከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀልም ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ