“አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የአማራ እና አፋር ክልሎችን በመውረር 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎችን ለችግር እንዲጋለጡ አደርጓል” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

189
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 20/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ አምባሳደሩ በመግለጫቸው እንዳሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ከረጅ ተቋማት ኀላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ እና አፋር አካባቢዎች ወረራ በመፈጸም በርካታ ሕዝብ እንዲፈናቀል ማድረጉንና ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አቶ ደመቀ ገልፀውላቸዋል ነው ያሉት አምባሳደር ዲና።
የእርዳታ ድርጅቶቹም ከእርዳታ ፍተሻ እና ከባንክ አገልግሎት፣ ከቪዛ እና ከኮምዩኒኬሽን መሣሪያዎች ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች ማቅረባቸውንም አንስተዋል።
መንግሥት እርዳታ እንዲደርስ ፍላጎት እንዳለው አቶ ደመቀ መግለጻቸውን አንስተዋል፡፡ ዓለምአቀፍ ለጋሽ ድርጀቶች ሰብዓዊ ድጋፍ በሚያደርጉበት ጊዜ ከሀገሪቱ ብሔራዊ ደኅንነት ጋር በማይፃረር መልኩ መሆን እንደሚገባውም አስገንዝበዋል ነው ያሉት፡፡
የእርዳታ ምግቦች በአሸባሪው ቡድን እጅ መገኘቱ የእርዳታ ድርጅቶች አሠራራቸውን ሊፈትሹ እንደሚገባም አቶ ደመቀ ማሳሰባቸውን አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ እና አፋር ክልል በርካታ ንጹሐንን በጅምላ ገድሏል፣ ንብረቶችን አውድሟል፣ ዘርፏል፡፡ በዚህም 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሕዝብ ለችግር መጋለጡን አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው ጠቅሰዋል፡፡ ለችግር ከተጋለጠው ሕዝብም ከ500 ሺህ በላይ ሕዝብ መፈናቀሉንና አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ለተራድኦ ድርጅቶቹ ተገልፆላቸዋል ብለዋል።
በሳምንቱም በውጭ ሀገራት በችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደሀገራቸው መመለስ ተችሏል ተብሏል። የጸጥታው ምክርቤት በአየርላንድ ጥያቄ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ጉዳይ በዝግ እንደሚመክርም ተመላክቷል፡፡
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ የልዩ ኀይል ምልምል ሠልጣኞችን እያስመረቀ ነው፡፡
Next articleአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወደ ጦርነት የማገዳቸው የትግራይ ወጣቶች እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ የተማረኩ የአሸባሪ ቡድን አባላት ጥሪ አቀረቡ፡፡