
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 20/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ የልዩ ኀይል ምልምል ሠልጣኞችን እያስመረቀ ይገኛል፡፡
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው፣ የአማራ ክልል የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ቢሮ ኀላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶክተር)፣ የአማራ ክልል ልዩ ኀይል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ሠልጣኞቹ በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ በጥሩብርሃን መሰረታዊ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን ሲወስዱ የቆዩ ናቸው፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ