
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአቶ ደረጀ ሀብተወልድ አስተባባሪነት የዜና ቲዩብ ቤተሰቦች ከ1 ነጠብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና ለተፈናቃዮች ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ድጋፉ በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ለመከላከያ የሠራዊት አባላት የሚዉል ነዉ፡፡
ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ ደረጀ ሀብተወልድ በሀገር ዉስጥ እና በባሕር ማዶ የሚገኙ የዜና ቲዩብ ቤተሰቦች ያደረጉት ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይ በዚህ ወቅት መረዳዳት እና መደጋገፍ እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ደረጀ የዜና ቲዩብ ቤተሰቦች ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና ለተፈናቃይ ወገኖች አለናችሁ ብለዋል፡፡ ለዚህም ምስጋናየን አቀርባለሁ ነዉ ያሉት፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ዶክተር ኢንጅነር ከማል ሙሀመድ አቶ ደረጀ ሀብተወልድ እና የዜና ቲዩብ ቤተሰቦች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡ ሌሎች ወገኖችም ድጋፋቸዉን አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል ከንቲባዉ፡፡


ዘጋቢ፡- አንዋር አባቢ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ