“ኦነግ ሸኔ ከወለጋ ሕወሓት ከቆቦ አፈናቅሎኛል” በሁሉቱ አሽባሪዎች የተፈናቀሉት እናት

402
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ወይዘሮ አያልነሽ ፋስሃ የአራት ልጆች እናት ናቸው። ከራያ ቆቦ ተፈናቅለው ደሴ ከተማ አዲስ ፋና ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ነው ያገኘናቸው፡፡
“ከዛሬ ሦስት ወር በፊት ኦነግ ሸኔ ባደረሰብን ጥቃት ተፈናቅየ ከወለጋ ወደ ራያ ቆቦ ነው የመጣሁት” የሚሉት ወይዘሮ አያልነሽ፤ አሁንም በአሸባሪው ሕወሓት ከራያ ቆቦ ተፈናቅለው ወደ ደሴ መምጣታቸውን ይናገራሉ፡፡
ከዛሬ ሦስት ወር በፊት በኦነግ ሸኔ ጥቃት ልጆቻቸውን ይዘው ራያ ቆቦ መምጣታቸውን ያስታውሱት ወይዘሮ አያልነሽ፤ አሁን ደግሞ የአሸባሪውን ሕወሓት ጥቃት በመሸሽ ወደ ደሴ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡
ከራያ ቆቦ ተፈናቅለው ወደ ደሴ ሲመጡም ነብሰ ጡር መንገድ ላይ ሲወልዱ፣ እሳቸውን ጨምሮ ልጅ ያዘሉትና የያዙት እናቶች እየወደቁ እየተነሱ አድካሚና አሰልቼ በሆነ መልኩ በእግር ከተጎዙ በኋለ መርሳ መድረሳቸውንና ከመርሳ በትራንስፖርት ደሴ መድረሳቸውን ነግረውናል፡፡
“አሸባሪው ሕወሓት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ባደረሰው ጥቃትም የሰው ህይወት አልፏል፤ እኛም በፈጣሪ ዕገዛ እዚህ ደርሰናል” ብለውናል፡፡
እሳቸው በቆዩበት ራያ ቆቦ በአሸባሪው ቡድን የ14 ዓመት ልጅ እና መነኩሴዎች ሳይቀር መድፈራቸውን ገልጸው፤ የእሳቸው ቤተሰቦችም ግማሹ ራያ ቆቦ፣ ከፊሉ በወልዲያ፤ ግማሹ በመርሳ ተበታትነው የሚገኙ በመሆናቸው ምን እንደደረሰባቸው እንደማያውቁና በጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን ነግረውናል፡፡
ሀገር በጥባጩ አሸባሪ ቡድን ተደምስሶ እንደ እርሳቸው ያሉ አርሶ አደሮች ወደግብርናው፣ ነጋዴውም ወደ ንግዱ፣ ተማሪውም ወደ ትምህርቱ እንዲመለስ ምኞታቸው መሆኑን ነግረውናል። ኢፕድ እንደዘገበው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየደቡብ ዕዝ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን ሲሰሩ በነበሩ የሰራዊቱ አባላት ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጠ።
Next articleየዜና ቲዩብ ቤተሰቦች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ፡፡