
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሚሊሻ አለሙ ላቀው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንኮበር ወረዳ የማህል ወንዝ ቀበሌ ነዋሪ ነው።
ወራሪውና ተስፋፊው ትህነግ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ሰርጎ በመግባት በሰውና በንብረት ላይ እያደረሰ ያለውን ውድመት በሰማሁ ጊዜ አራት የቤተሰብ አባላት ቢኖረኝም ግንባር ከመሄድ የሚያግደኝ ምንም ነገር የለም፤ ከሀገር አይበልጥም በማለት ነው ወደ ግንባር ያቀናሁት ብሏል።
ሚሊሻ አለሙ ላቀው ጠላትን ለመፋለም ወደ ግንባር ባቀናበት ጊዜ ታጥቆት የነበረው የጦር መሳሪያ ኋላቀር ሲሆን በወቅቱ ከመከላከያ ጋር በመሆን ከጠላት ጋር ሲፋለም ጥይት ይጨርሳል።

እንደ ሚሊሻ አለሙ ላቀው ገለፃ “ጥይት ጨርሻለሁ ብዬ መሸሽ አልፈለኩም፤ ይልቁንስ ከጠላት በመማረክ ይህን ስግብግብ ቡድን ድል ሳላደርግ አልመለስም” የሚል ወኔን ተላብሸ ምሽግ ላይ እራሴን ለትንቅንቅ አዘጋጅቼ መጠበቅ ጀመርኩ ይላል።
ሚሊሻ አለሙ ብዙም ሳይቆይ ጠላት ወደ ምሽግ ሲጠጋ ትንቅንቅ በማድረግ ጠላትን በድንጋይ በመምታት ከጣለው በኋላ የያዘውን መሳሪያ ነጥቆ ጠላትን በመደምሰስና ሙሉ ትጥቁን በመማረክ አኩሪ ጀብዱ ፈፅሟል።

አሁን ላይ “ከጠላት የማረኩትን መሳሪያና ሙሉ ትጥቅ በመያዝ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ይህ ጠላት እስኪቀበር እዋጋለሁ” ሲል ሚሊሻ አለሙ ላቀው ገልፆልናል። መረጃው የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ