“የአሸባሪው ቡድን አባላት ትግራይ የኢትዮጵያ አይደለችም የሚሉ ጽሑፎችን በየግድግዳው ጽሕፈው ሄደዋል” ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ ጥላሁን በሰሜን ምዕራብ እዝ የኮር አንድ አዛዥ

454
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በጋይንት በኩል የማጥቃት እርምጃ የተወሰደባቸው የአሸባሪው ቡድን አባላት “ትግራይ የኢትዮጵያ አይደለችም” የሚል ጽሑፎችን በየግድግዳው ጽሕፈው መፈርጠጣቸውን ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ ጥላሁን ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን የሕዝቡን ሀብት ጨምሮ በርካታ መሠረተ ልማቶችን እንዳወደመም ተናግረዋል፡፡
በሰሜን ምዕራብ እዝ የኮር አንድ አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ ጥላሁን ትላንት በነፋስ መውጫ ጨጨሆ ግንባር ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ አሸባሪው በሰሜን ጎንደር በተለይም በጋይንት በኩል አድርጎ ወደ ደብረ ታቦር ለመግባት ያደረገው ሙከራ ከሽፎበት የማጥቃት እርምጃ ተወስዶበታል፡፡
ቡድኑ ባለፈባቸው አካባቢዎች ሁሉ “ትግራይ የኢትዮጵያ አይደለችም”፤ “ኢትዮጵያ የኛ አይደለችም” የሚሉ የጽሑፍ መልዕክቶችን በየግድግዳው ላይ ጽሕፎ መሄዱን ያስታወቁት ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ፤ ይህ ምን ያህል ሀገር ጠል ቡድን መሆኑን ያመላከተ ነው ብለዋል።
እንደ ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ ገለጻ፤ አሸባሪው ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች ሁሉ ኢትዮጵያ ጠል መሆኑን በግልጽ አሳይቷል፡፡ ኢትዮጵያ የኛ አይደለችም ከሚለው መልዕክቱ ባሻገር፤ በጋሳኝ፣ በክምር ድንጋይና ነፋስ መውጫ፤ የግለሰብ ንብረት ዘርፏል፡፡
የሕዝቡን ሀብት ጨምሮ በርካታ መሠረተ ልማቶችን አውድሟል፡፡ ዓላማውም ማውደም ስለሆነ ጸረ መንግሥት መሆን ብቻ ሳይሆን ጸረ ሀገርና ጸረ ሕዝብ መሆኑንም አሳይቷል፡፡
በዚህ መሠረት ሱቆችንና ድሆች የሚጠቀሙበት ዕለታዊ ፍጆታቸውን ሳይቀር በመዝረፍ ሰብዓዊ ቀውስ ማድረሱን ገልጸዋል።
ብርጋዴር ጀኔራል ብርሀኑ ፤ ለዚህ ምላሽ ሠራዊቱ አሸባሪውን እየቀጣ በአሁኑ ወቅትም በነፋስ መውጫ ጨጨሆ ግምባር ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ ኢፕድ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“አሸባሪውን ትህነግ ከእነ አስተሳሰቡ ቀብረን ኢትዮጵያን እናስቀጥላለን” አቶ ተመስገን ጥሩነህ
Next article❝እንኳንስ ሰዎቹ ዘማቾች ናቸው ግመሎቹ❞