ሕዝቡ እያደረገልን ላለው ድጋፍ አሸባሪውን የትህነግ ቡድን በመደምሰስ እንክሰዋለን ሲሉ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኀይል አመራሮች እና አባላት ገለጹ፡፡

265
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፌደራል መንግሥት የሰጠውን የጥሞና ጊዜ እንደ ክፍተት በመጠቀም አሸባሪው ትህነግ በአማራና አፋር ክልል ላይ ወረራ ፈጽሟል፡፡ በዚህም የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኀይል በተሰጠው ግዳጅ መሰረት የአሸባሪ ቡድኑን አከርካሪ በመስበር ላይ ይገኛል፡፡ ሕዝቡም አሸባሪውን ቡድን ለማጥፋት እየተከናወነ ያለውን ዘመቻ በመደገፍ ላይ ነው፡፡
ሕዝቡ እያደረገልን ላለው ድጋፍ አሸባሪውን የትህነግ ቡድን በመደምሰስ እንክሰዋለን ሲሉ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኀይል አመራሮች እና አባላት ገልጸዋል፡፡
ሌተናል ኮሎኔል ጫልቺሳ ከበደ እንዳሉት ሁሌም ለዚህ ቀናዒ ለሆነ ሕዝብ አይደለም አንድ ጊዜ ከዛ በላይ ቢሰውለት ቢያንሰው እንጂ አይበዛበትም፡፡ የሽብርተኛው ቡድን ግብዓተ መሬት እስኪፈፀም ድረስ የበኩሌን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ ነኝ ብለዋል፡፡
ሻለቃ ፍቅሬ ድሪባ በበኩላቸው ሽብርተኛው እና ግብረ አበሮቹ ሽንፈታቸውን መቀበል ሲሳናቸው የሐሰት የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እያካሄዱ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ ሕዝቡ የሽብር ቡድኑ ለሚነዛው የሐሰት ወሬ ጆሮ መስጠት እንደሌለበትም ገልጸዋል፡፡
ሕዝቡ ለሠራዊቱ ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንዲቀጥል የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኀይል አባላት ጥሪ ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝እናንተ ቆጥባችሁ እንዳልሰጣችሁን ሁሉ እኛም ያለንን አንቆጥብም፤ ውድ ሕይወታችንን ከፍለን የሀገራችን ታሪክ እናስከብራለን❞ የ13ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ሀሸም መሐመድ
Next article“አሁን የመስጠት ጊዜ ነው፤ ኢትዮጵያን ለማትረፍና እንደ ሕዝብ ለመትረፍ በአንድ ላይ የምንቆምበት ጊዜ አሁን ነው” ዶክተር ሙሉነሽ አበበ