ደግነት በተግባር ሲገለጽ…

185
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ወይዘሮ ደስታ ወልደሰማያት በኮምቦልቻ ከተማ ነው የሚኖሩት፡፡ በከተማዋ ያስገነቡትን አዲስ ሕንፃ በአሸባሪው ትህነግ ወረራ ከሰሜን ወሎ ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች አገልግሎት እንዲውል አድርገዋል። ወይዘሮ ደስታ ለጋስነታቸውን እና መልካምነታቸውንም በተግባር ገልጸዋል። ወይዘሮዋ በኮምቦልቻ ከተማ ያስገነቡትን አዲስ ባለ አራት ወለል ሕንፃ በወር ከ250 ሽህ ብር በላይ በኪራይ ያገኙበታል፡፡ ይሁን እንጅ ሁሉም ነገር ከወገን አይበልጥም ያሉት ወይዘሮ ደስታ ለተፈናቃይ ወገኖች ማረፊያ ይሆን ዘንድ አበርክተዋል። ወይዘሮ ደስታ ለወገኖቻቸው በዚህ መልኩ መደገፍ በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውንም ለአሚኮ ተናግረዋል።
ሌሎችም በዚህ የችግር ወቅት ከወገናቸው ጎን ባላቸው ነገር ሁሉ እንዲቆሙ ጠይቀዋል። ከ74 በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃዮች ሕንጻው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
በአሸባሪው ቡድን ወረራ ምክንያት ተፈናቅለው ኮምቦልቻ የሚገኙት ወይዘሮ ትዕግስት ይደጉ እንደተናገሩት ወይዘሮ ደስታ ተፈናቃዮችን ቤት የእግዚአብሔር ነው ብለው ተቀብለውናል፤ ለተደረገልን ድጋፍም ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡-አንዋር አባቢ-ከኮምቦልቻ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የሕልውና ዘመቻውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ኅብረተሰቡ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል” ዶክተር ሙሉነሽ አበበ
Next article❝እናንተ ቆጥባችሁ እንዳልሰጣችሁን ሁሉ እኛም ያለንን አንቆጥብም፤ ውድ ሕይወታችንን ከፍለን የሀገራችን ታሪክ እናስከብራለን❞ የ13ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ሀሸም መሐመድ