
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትህነግ የከፈተውን ወረራ ተከትሎ የሕልውና ዘመቻውን በድል ለማጠናቀቅ የተለያዩ ኮሚቴዎች ተዋቅረው እየሠሩ ነው፡፡ ከነዚህም ኮሚቴዎች አንዱ የስንቅ ዝግጅቱን የሚመራው ነው፡፡ ይህ ኮሚቴ የሕልውና ዘመቻውን በድል ለማጠናቀቅ 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የሚገመት ሃብት ለማሰባሰብ አቅዶ እየሠራ ነው፡፡
ይሁን እንጅ አሸባሪው ቡድን ከከፈተው ወረራ አንጻር ሲታይ ከታቀደው በላይም መሰብሰብ አስፈላጊ ሆኖ እንደተገኘ ነው በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ አበበ (ዶክተር) የገለጹት፡፡
ዶክተር ሙሉነሽ እንዳሉት እስካሁን ኅብረተሰቡ ሰፊ ርብርብ እያደረገ ቢሆንም የተሰበሰበው ከእቅዱ በታች መሆኑን አንስተዋል፡፡ ለዚህም በምክንያትነት አሸባሪው ቡድን በገባባቸው አካባቢዎች ያደረሰው ጉዳት ሰፊ በመሆኑ የሚሰበሰበውን ስንቅ በሚፈለገው ደረጃ እንዳይሆን አድርጎታል ነው ያሉት፡፡ በመሆኑም የሕልውና ትግሉን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ኅብረተሰቡ የሚያደርገው ድጋፍ ከመቸውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m