“ከቀደምት አባቶቻችን የተረከብናትን ሀገር ሉዓላዊነት ለማስቀጠል እንታገላለን” ምልምል ሴት የሠራዊት አባላት

523

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከቀደምት አባቶቻችን የተረከብናትን ሀገር ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሕይወት መስዋእትነት በመክፈል ጭምር እንታገላለን ሲሉ በጦላይ ማሰልጠኛ ማዕከል መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ላይ የሚገኙ ምልምል ሴት የሠራዊት አባላት ገለጹ።

ለኢዜአ ሐሳባቸውን ያጋሩት ሴት ምልምል የሠራዊት አባላት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ፍጹም ኢትዮጵያዊነት የሚንጸባረቅበት ተቋም ነው ይላሉ። ይህም “ከራስ በፊት ለሕዝብ” የሚለውን መርህ በመላበስ ለሀገር ሉዓላዊነትና ለሕዝብ ሰላም መጠበቅ መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል።

ምልምል ወታደር ብዙ ዓለማየሁ ኢትዮጵያ ለዘመናት ሉዓላዊነቷ ተከብሮ የቆየች፤ ታሪክ ያላቸው ሕዝቦች ሀገር ባለቤት ነች ስትል ገልጻለች።

የአሁኑ ትውልድም የአባቶቹን የቃልኪዳን አደራ በመረከብ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ማስረከብ ይጠበቅበታል ብላለች።
የኢንጂነሪንግ ተማሪ እንደነበረች የገለጸችው ምልምል ወታደሯ ለሀገር ሉዓላዊነት መጠበቅ የበኩሏን ለመወጣት መስዋእትነት ለመክፈል መዘጋጀቷን አረጋግጣለች።

ምልምል ወታደር ኢማን ዋሱ በበኩሏ ኢትዮጵያ ከአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ነፃ እንድትወጣ በመሻት የአገር መከላከያ ሠራዊቱን መቀላቀሏን ገልጻለች።

ለሀገሬ አለሁላት የምትለው ኢማን ቀደምት አባቶች ያስረከቧትን ሉዓላዊነቷ የተጠበቀች ሀገር ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን ተናግራለች።

ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ለሀገር ሉዓላዊነት መከበር የመከላከያ ሠራዊቱን በመቀላቀል ለሀገራቸው ዳር ድንበር መከበር እንዲተጉም ጥሪዋን አቅርባለች።

ለሀገር ሉዓላዊነት መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኗን የገለጸችው ደግሞ ምልምል ወታደር መቅደስ ታምሬ ነች።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአሸባሪውን የትህነግ ቡድን እስከመጨረሻው ለማስወገድ መተባበር እንሚገባ በደባርቅ ከተማ የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ገለጹ።
Next articleየአሸባሪው ትህነግ ወረራ ለመመከት መስዋእትነት እየከፈሉ ላሉ ጀግኖች መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ገለጹ።