
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በጀግናው መከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ የጠላት ኀይል ተመክቶና ተመትቶ ወደ መጣበት መንገድ ሙትና ቁስለኛውን እያንጠባጠበ መፈርጠጡን ጀምሯል።
የአሸባሪው ሕወሓት ሌተናል ኮሎኔል ገብረህይወት ገብረአላፍ ከጋሳይ ግንባር የወገን ጦር መድረሻ ሲያሳጣው እጁን ለመከላከያ ሠራዊት ሰጥቷል።
ሌተናል ኮሎኔሉ አራት የተለያዩ መታወቂያዎች በፍተሻ ተይዞበታል። በርከት ያሉ የባንክ አካውንቶችም ይዞ ተገኝቷል። ኮሎኔሉ የሚመራው ጦር እንደተበተነና ተስፋ በመቁረጥ ስርዓት የማፍረስ ተልዕኮ መያዙንም ተናግሯል።


ዘጋቢ:- ብሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ