የደብረ ታቦር ወጣቶች ግንባር ድረስ በመሰለፍ ደጀንነታቸውን እያሳዩ ነው።

292
ባሕር ዳር: ነሐሴ14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ታቦር ወጣቶች ግንባር ድረስ በመሰለፍ ደጀንነታቸውን እያሳዩ ነው። የደብረ ታቦር ነዋሪ ዓባይነው አሸብር ወጣቱ በግንባር ለተሰለፈው ሠራዊት ስንቅ በማቀበል፣ ሰርጎ ገቦችን አንቆ በመያዝና ለጸጥታ አካላት በማስረከብ፣ በግንባር በመሰለፍ እና ተደራጅተው ሌት ከቀን አካባቢያቸውን በመጠበቅ ላይ እንደሆኑ ተናግሯል።
አሸባሪው ትህነግ ሀገሪቱን ለመጨቆን በሴራ በገባበት ወቅት በደብረ ታቦር፣ በጉና፣ በፋርጣና በአካባቢው ኅብረተሰብ የደረሰበትን ኪሳራ አይረሳውም ነው ያለው።
“ቡድኑ በአካባቢው ኅብረተሰብ ደርሶበት የነበረውን ሽንፈት አሁን መበቀል ይፈልጋል፣ የደብረ ታቦር ወጣቶችም ይህን ስለሚያውቁ የሽብር ቡድኑን ድጋሜ ለመቅበር እየሠሩ ናቸው” ብሏል። የደብረ ታቦር ወጣቶችና የአካባቢው ማኅበረሰብ የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ነው ወጣቱ የተናገረው። ወጣቱ ብቻውን ሳይሆን በየደረጃው ከሚገኙ የጸጥታ አካላት ጋር ተባብሮና ተናብቦ እየሠራ እንደሆነም ገልጿል።
ሌላው የከተማዋ ነዋሪ ወርቅዬ ፈንታው ወጣቱ በመደራጀት የተመደበበትን ሥራ እያከናወነ ነው ብሏል። የደብረ ታቦር ወጣቶች ሰርጎ ገቦችንና የጠላት አሉቧልታንም እየታገሉ እንደሆነ ነግሮናል። በየአካባቢው የሚገኙ ወጣቶች ከደብረ ታቦር ወጣቶች ብርታትን፣ አንድነትን፣ ጀግንነትንና ጥንካሬን መውሰድ እንዳለባቸው ጠቅሷል።
“ደብረ ታቦር ሲነሳ ግራር ይነሳል መሀል ደብረ ታቦር ላይ ግራርን የማያውቅ የለም። ጠላት ደብረ ታቦርን ያዝኩ እያለ ያስወራል ይኸው እኛ ያለነው ግን ግራሩ ስር ነው። ስለዚህ ሁሉም የሀገራችን ሕዝቦች በአሸባሪው ትህነግ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ መታለል የለባቸውም” ብሏል።
“አሸባሪው ትህነግ የደብረ ታቦርን ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቀዋል፤ ጠላትን ለመቅበር ግንባር ነው ያለነው፤ ደብረ ታቦርን ይመኟታል እንጂ አያገኟትም” ያለው ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ ወጣት መስፍን ኃይሉ ነው።
በረከት አዲሱ የተባለ የከተማዋ ነዋሪ “ጠላት የደብረ ታቦር ወጣቶች ከከተማዋ ወጥተዋል እያለ ያስወራል አንድም ወጣት የወጣ ግን የለም። ወጣቱ ከተማዋን ብቻ ሳይሆን በየዙሪያው ጠላትን ነቅቶ እየጠበቀ እንደሆነም ነው የገለጸው።
አሸባሪው ቡድን እስኪደመሰስ ወጣቱ ሌት ከቀን አይተኛም ብሏል። በግንባር ለሚዋደቁ ጀግኖች ቡና ሳይቀር እያቀረቡላቸው እንደሆነም ተናግሯል። የደብረ ታቦር ወጣቶች እየሰሩት ያለው አኩሪ ተግባር ነገ ታሪክ የሚዘክረው ይሆናል ብሏል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ- ከደብረ ታቦር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleቺርቤዋ ፡ ናሲ 15/2013 ም.ዓ እትሜት
Next article“በሉዓላዊነታችን ላይ የተቃጣውን የባንዳ ጥቃት ለመቀልበስ እንደ አባቶቻችን ሁሉ እኛም በአንድ መንፈስ ለአንድ ዓላማ ሁሌም በፅናት ልንቆም ይገባናል” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ