
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በትግራይ ካለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ሁኔታውን የሚዘግቡበት መንገድ መለያየትን የሚያባብስና ኀላፊነት የጎደለው ሆኖ መታየቱን ሩሲያ አስታውቃለች።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማርያ ዛካሪቫስ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የህልውና ዘመቻና ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
ቃል አቀባይዋ በመግለጫቸው አሸባሪው ህወሃት አሁንም ድረስ ወደ ውጊያ በመግባት ወደ አማራና አፋር አጎራባች ክልሎች ወረራ በመፈጸም የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲስተጓጎል ማድረጉንና የኢትዮ-ጂቡቲን መስመር ለመዝጋት ጥቃት መፈጸሙን ገልጸዋል።
“ቡድኑ ከክልሉ በማለፍ ያደረሰው ጭፍጨፋና ጥቃት ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈለጋቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ድጋፍ እንዳያገኙ አድርጓል” ብለዋል።
“ለእነዚህ ችግሮች መከሰት የአንዳንድ የምዕራባውያን የሚዲያ አካላት ሚናም ከፍተኛ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል” በማለት ያብራሩ ሲሆን፤ የእነዚህ አካላት እንቅስቃሴ ሰላምን ከማምጣት ይልቅ ኅላፊነት በጎደለው ተግባር ጥፋትን ማባባስና ልዩነቶችን የማቀጣጠል ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
“በትግራይ ክልል ሰላምን ለማምጣትና ወደ መደበኛ የህይወት እንቅስቃሴ ለመመለስ በኢትዮጵያ መንግሥት እየተከናወነ ያለውን ሕግ የማስከበር ተግባር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲደግፍም ጥሪ አቅርበዋል።
“ሩሲያ ኢትዮጵያውያን የውስጥ ጉዳያቸውን ከአፍሪካውያን ጋር በራሳቸው ለመፍታት ወሳኝ ሚና መጫወት አለባቸው ብለን እናምናለን” ሲሉ መግለጻቸውን በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አስታውቋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m