በአሸባሪው ቁንጮ ፃድቃን ገ/ትንሣይ የሚመራው የጠላት ኅይል በመከላከያ ሠራዊታችን ተመታ።

289
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው ቁንጮ ፃድቃን ገ/ትንሣይ የሚመራው የጠላት ሀይል፣ በሰሜን ወሎ ግንባር በተሰማራው የመከላከያ ሠራዊታችን ተመቷል።
ዓርሚ ሁለት የሚባልና በከሀዲው ሜ/ጄ/ል ዮሐንስ በቅፀል ስሙ ጆን፣ በምክትሉ ከሀዲው ማዕሾ በየነ እና ከሀዲው ከበደ ፍቃዱ እንዲሁም በሜካናይዝድ አዛዡ ከሀዲው ኮ/ል ገ/ስላሴ የተመራው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ኅይል ድባቅ ተመቷል።
በግንባሩ የተሰማሩ ሁለት ክፍለ ጦር አዛዦ እንደተናገሩት፤ መንግሥት የተናጠል የተኩሥ አቁም እርምጃውን ካነሳ በሁዋላ ከበላይ በተሠጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ጋሸናን ዋና ማዕከል በማድረግ ከዋድላ እሥከ ላሊበላ መስመር ላይ የነበረውን የአሸባሪውን ኅይል መደምሠሳቸውን አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ሰዓት ጠላት በጀግኖቹ የሠራዊት አባላት፣ ልዩ ኅይል እንዲሁም የሚሊሻ አባላትና የአካባቢው አርሶ አደር ከበባ ውሥጥ ሆኖ ይገኛል።
ይህ የተዳከመ የጠላት ኅይል በጋሸና፣ በመቄት፣ በሙጃ፣ በንፋሥ መውጫ አካባቢዎች እየተመታና እየተበተነ ይገኛል ብለዋል።
በነዚህ አካባቢዎች በጠላት ላይ በተደረገ ጥቃት 3 ድሽቃ፣ 6 ሺ የድሽቃ ጥይት፣ 87 የዕጅ ቦንብ፣ 229 ክላሽንኮቭ ነፍስ ወከፍ መሣሪያ፣ 5ሺ የክላሽ ጥይት፣ አንድ የጦርሜዳ መነፅር ሢማረክ ፣ በርካታ ቁጥር ያለው የሠው ሀይል እና ጠላት ይጠቀምባቸው የነበሩ 2 መድፎች እንዲሁም አንድ ዙ 23 መደምሠሥ መቻሉን ዋና አዛዦቹ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በደሴ ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች የሚውል የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
Next article“በኢትዮጵያ መንግሥት እየተከናወነ ያለውን ሕግ የማስከበር ተግባር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲደግፍ ጥሪ እናቀርባለን” ሩሲያ