
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ላይ ወረራ እያካሄደ የሚገኘው የትህነግ ሽብር ቡድን በደቡብ ጎንደር ዞን በከፈተው ውጊያ ከሀገር መከላከያ፣ አማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ እየደረሰበት ያለውን ኪሳራ መቋቋም ሲያቅተውና በተስፋ መቁረጥ ትናንት ወደ ደብረታቦር ከተማ አራት ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ጥቃት መፈጸሙን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በጥቃቱም የአንድ ቤተሰብ አባላት የነበሩ 3 ሴቶችና 2 ወንዶች ለህልፈት ተዳርገዋል፤ ከዚህ ውስጥ አንድ ሕጻን ይገኝበታል፡፡ በጥቃቱም 2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት እንደደረሰና ግምቱ ያልታወቀ የግለሰቦች ንብረት መውደሙን ከተማ አስተዳደሩ እንደገለጸ ዘግበናል፡፡
ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ንጹሐንን ዒላማ አድርጎ ጥቃት እየፈፀመ የሚገኘውን አሸባሪውን ትህነግ እንዲያወግዝ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡ በዚህም አሸባሪው ትህነግ በደብረታቦር የፈጸመውን የሽብር ጥቃት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያወግዝ የትዊተር ዘመቻ ተካሂዷል፡፡
ዘመቻው #DebreTabor የሚለውን ሐሽታግ በመጠቀም በርካታ የትዊተር መልዕክቶች በኢትዮጵያውያን ወገኖች የተሰራጨበት ነበር። ከ12 ሺህ በላይ ትዊቶች በኢትዮጵያ፣ በአሜሪካ፣ በብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ፊንላንድ እና በሌሎችም ሀገራት ተደራሽ ሆኗል።
በዕለቱ ትዊት ከተደረጉ ሃሽታጎች ውስጥ






#TPLFisGenocider NotVictim #Amharas
TPLFisTheCause!
#NoNegotiation WithTPLF
#GalicomaMassacre የሚሉት ይገኙበታል፡፡