
” ከድሮም እንደዚሁ ነበሩ. .. እየዞሩ ያገኙትን ሁሉ ይዘርፉ ነበር ፤ የስኳር ፋብሪካ ገብተው ማሽኖቹን እንዳለ ነቃቅለው ሱዳን ወስደው ሽጠዋል ” ብርጋዴር ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ
ስለአሸባሪው ትህነግ ባሕል ከተነሳ እንዲህ ያገኙትን መዝረፍ ልከኛ መገለጫው ነው። በሽምቅ ውጊያ የተለማመዱት ዘራፊነት መንግሥት ሆነውም ያልተላቀቃቸው እውነት ሆኖ ከለውጡ ማግስት ሀገር ያስገረመ ዝርፊያ ተግባር ተሰምቷል። ከግለሰብ ማጀት የጀመረ ልማድ እስከ ሀገር በጀት የቀጠለ ነው።
ለአብነት ያህል ከአማራው ባለሀብት ተዘርፎ ትእምት የሚሉት የዝርፊያ መሳሪያቸው ንብረት የተደረገውን ባለሀብት ታሪክ መነሻ ማድረግ በቂ ነው። የአዲስ መድኃኒት ፋብሪካ ጠንሳሽና በኋላም የ60 በመቶ ባለድርሻ የነበሩት አቶ ሙሉጌታ ጓዴ ሙሉ በሙሉ ድርሻቸው በሕወሓቱ ኤፈርት የተነጠቁ ባለሀብት ናቸው። ታሪካቸውን በነሐሴ 10/2010 ለኢሳት በነገሩበት ታሪክ የወያኔን አይን ያወጣ ዘራፊነት የሚመሰክር ነው። አቶ ሙሉጌታ ጓዴ ትህነግ የመራው ኃይል ስልጣን ላይ ሲወጣ የመድኃኒት ፋብሪካ ለማቋቋም አቅደው በወቅቱ ለፋብሪካቸው ፈቃድ ለማውጣት እክል ሲገጥማቸውና እንደማይቻል ሲነገራቸው የዘራፊው ቡድን መሪ ከነበረው ስብሃት ነጋና ሌሎች ሽርክና ጠይቀው ስብሃት ያመጣው ሰው ፕሮጀክቱን በሽርክና ሲቀላቀል ፈቃድ አግኝቷል። ፋብሪካው ሲታቀድ ድሬዳዋ ወይንም አስመራ የነበረ ቢሆንም የትህነግ አመራሮች ሲገቡበት ወደ አዲግራት መወሰዱን ገልጸዋል። ስብሃት ነጋ ያመጣው ሰው 40 በመቶውን ሲይዝ አቶ ሙሉጌታ ጓዴ 60 በመቶ ይዘው ስራው እንዲቀጥል ተደረገ።
በሂደትም የግለሰቡ ድርሻ ወደ ኤፈርት እንዲዛወር መደረጉንና በኋላም በግፊትና በጫና ከሳቸውም ድርሻ ኤፈርት 11 በመቶ በመውሰድ ከግማሽ በላይ ወሰደ። በዚህ የድርሻ የበላይነት የወሰደው ዘራፊ ቡድን ባለሀብቱን ከድርሻው አስወጥቶ ከሀገር እንዲወጡ አደረገ። በአሜሪካና በእንግሊዝ ፍርድ ቤቶች ክስ መስርተው ሲሟገቱ የኖሩት አቶ ሙሉጌታ ዛሬም ድረስ ምላሽ ያጡ የዘርፊያ ፖለቲካ ሰለባ ናቸው።
ለዓመታት የዘለቀው የሙሉጌታ ዓለምአቀፍ የሕግ ክርክር መልስ ሳያገኝ ወያኔ ለሃያ ዓመታት በሰው ላብ የተገነባ ፋብሪካን ነገደበት። አተረፈበት። እንደዚህ ያሉ ከግለሰብ ላብ ላይ የተቀሙ ባለሀብቶች ታሪኮች አያሌ ናቸው። ትግራይ ላይ ካልሠራችሁ እየተባሉ ከሀገር የወጡ ባለሀብቶችም ብዙ ናቸው። ዝርፊያን ጌጥና ብልጠት ያደረገው ኃይል ገና ደርግ ወድቆ ስልጣን ላይ ሳይወጣ የት አካባቢ ምን ንብረት እንዳለ በካርታ ላይ ለይቶ ሀገር ሲቆጣጠር በዘመኑ ነበረ የሚባልን ቁሳቁስ ሁሉ ወደ መቀሌ ሲያጓጉዝና ሲጭን ነበር። ከ1983 በኋላ በአማራ ጀነሬተር ያልተነቀለበት ከተማ ማግኘት ቀላል አይደለም።
በተለይ ግን በጣሊያን መንግሥት ድጋፍ በበለስ ተፋሰስ ይሠራ የነበረው የልማት ፕሮጀክት ዝርፊያና ውድመት የትግራይ ዘራፊ ልሒቅ ያለውን ስር የሰደደ የዝርፊያ ፖለቲካ እና ምቀኝነት ማሳያ ነው። 300 ሺህ ሔክታር ለማልማት የሜካናይዝድ እርሻ ፣ የዓሳና ከብት እርባታ ልማት እንዲመክን አድርጎታል። 17 ቀበሌዎችን የሚያበሩ 16 ጀነሬተሮች እና ከ300 በላይ ትራክተሮች ተነቅለው ተወስደው የበለስ ተፋሰስ ልማት ፕሮጀክት ዳዋ ውጦት ቀረ።
ደቡብ ኦሞ ላይ በተመሳሳይ ለዛሬው የስኳር ልማት መነሻ የነበረ የሜካናይዜሽን ማሽነሪና ሀብት ወደ ትግራይ ሊጫን ሲል ሕዝብ ተሰልፎ እንዳስቀረው በቅርቡ በአርትስ ቴቪ እንግዳ የነበሩት መቶ አለቃ ጳውሎስ መስክረዋል።
በአዲስአበባ የዳቦ ማሽነሪ፣ በድሬዳዋ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ፣ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የነበሩ የዕቃ መጋዘኖችና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ሁሉ በዚሁ ስግብግብ ጁንታ ተዘርፈዋል። ሁሉም ሰው በየክልሉና በየከተማው የሚያስታውሰው የ1983 ማግስት የዝርፊያ ተግባር የትየለሌ ነው።
ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ እንዳሉት ያገኙትን ሁሉ መዝረፍ ሲፈጠሩ፣ ሀገር ሲመሩ፣ ዛሬም በወረራ ጊዜያቸው ያለ መለያቸው ነው። በደረሱባቸው የአማራ ከተሞችና ወረዳዎች ሁሉ የመንግሥት ተሽከርካሪና ንብረትን ሁሉ እየነቀሉ እየጫኑ ነው። የአርሶአደር እህል ወደ መቀሌ እየተጫነ ነው። የወልድያ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልድያ ሆስፒታል፣ ባንኮች፣ የጤናና ትምሕርት ተቋማት ሁሉ እየተዘረፉ ወደ ትግራይ እየተጓጓዙ ይገኛሉ።
የዝርፊያ ፖለቲካ አራማጁ ወራሪ አማራን ሰው አልባ ለማድረግ ይዞት በተነሳው እልኩ በደረሰበት የቁስ ርሀቡን ለማስታገስ ዝርፊያ መፈፀም ተያይዞታል። የደምና የቁስ ርሃብተኛን ለመመከት፣ ሽምቅ ጠብቆ ማስጣል እና እያንዳንዷን የአማራ መሬት እሳት እንዲሆንበት ማድረግ የጸጥታ ኃይላችን፣ ሕዝባችንና የኢትዮጵያ ልጆች በሙሉ ወቅታዊ ተልዕኮ ነው።

99
18 Shares
Like
Comment
Share