
ባሕር ዳር: ነሐሴ13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ወቅታዊ ክልላዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ መረጃ ሰጥቷል።
የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በሁሉም አውደ ግንባሮች ከፍተኛ ድል የተገኘ መሆኑን ተናግረዋል።
ጠላት መጠነ ሠፊ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበትም አቶ ግዛቸው አስታውቀዋል።
በዛሪማ ፣ በወልድያ አካባቢ፣ በጋይንትና ጋሸና አካባቢ በሽብርተኛው የትህነግ ቡድን ላይ ጠንካራ የማጥቃት ዘመቻ እየተካሄደ ነው ብለዋል። ጠላትን የመቆራረጥና የመምታት ተግባር መፈጸሙንም አቶ ግዛቸው ጠቁመዋል።
በጋይንት ግንባር ብቻ በርካታ የጠላት ኀይል መማረኩን አቶ ግዛቸው ተናግረዋል። አብዛኛው የጠላት ኃይል በገባበት መቅረቱንም ገልጸዋል። ጥቃቱን ለመመከትም የአየር ጥቃት መፈጸሙን ተናግረዋል።
የወገን ኃይል የጠላትን መግቢያና መውጫ በመዝጋት በሁሉም ግንባሮች ያደረገው ጀብድ ታሪክ የማይረሳው ነው ብለዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ