
የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ቀለመወርቅ ምህረቴ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጡት ማሳሰቢያ ቀጥሎ ቀርቧል።
የአማራን ሕዝብ ለመውረር በሀገር አጥፊው ኀይል አማካኝነት በውዴታም ሆነ በግዴታ ወደ አማራ መሬት የገባችሁ ሁሉ እጃችሁን ለመከላከያና ለአማራ ልዩ ኀይል እንድትሰጡ እናሳስባለን።
እጁን በሰላም ለሚሰጥ ተዋጊ ኀይል በዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሕግ መሰረት ምህረት የሚደረግለት እና ደኅንነቱ የሚጠበቅለት መሆኑን እንገልጻለን።
እጅ ለሚሰጡ ኀይሎች የአጭር ጊዜ ስልጠና በመስጠት ወደ ሚፈልጉት ቦታ በአግባቡ የምንሸኝ ይሆናል።