
ባሕር ዳር: ነሐሴ13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚገኙ ታዳጊ ኢትዮጵያውያን የቡሄ በዓልን በማስመልከት በታዳጊ ሶፊ አስተባባሪነት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር አካሂደዋል፡፡
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው የታዳጊ ሶፊ ብሎም የሁሉም ታዳጊዎች ሕልም እንዲሳካ ሁሉም ዜጎች ለግድቡ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ በታዳጊዎቹ ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመርኃግብሩ ላይ በቡሄ ጭፈራ የታጀቡ መልዕክቶችም ተላልፈዋል።



ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ