የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና የሃይማኖት አባቶች የመስቀል በዓል የሚከበርትን አካባቢ አጸዱ፡፡

215

ባሕር ዳር፡ መስከረም 16/2012 ዓ/ም (አብመድ) በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና የሃይማኖት አባቶች የመስቀል በዓል የሚከበርባቸውን አካባቢዎች ሲያጸዱ አርፍደዋል፡፡

በከተማዋ የቆየውንና ያለውን አብሮነት፣ መተሳሰብና አንድነት ለትውልድ ለማስተላለፍ በተግባር የአንደኛው ሃይማኖት ተከታይ ለሌላኛው ሃይማኖት ተከታይ አጋር መሆኑን ያሳዩበት ተግባር መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ቀደምም የደባርቅ ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በዓል ለማክበር በሚዘጋጁበት ወቅት የመስጅድና ሌሎችም የሶላት መስገጃ አካባቢዎችን ማጽዳታቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

ዘጋቢ፡- ደስታ ካሳ -ከደባርቅ

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ( ዶክተር) የመስቀል በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት መልእክት
Next articleኅብረተሰቡ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ሊከሰቱ ከሚችሉ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች ሊጠነቀቅ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡