በክምር ድንጋይ አንድ የአማራ ጀግና 11 የአሸባሪው ትህነግ ታጣቂዎችን ደመሰሰ።

759

ነገሩ እንዲህ ነው ፦

የአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ታጣቂዎች በክምር ድንጋይ ከተማ ወደ አንድ ግለሰብ ቤት በመሄድ ለማጥቃትና ለመዝረፍ ተዘጋጁ። ታጣቂዎች ግለሰቡ ቤት ደረሱ።

ይህንን ቀድሞ የተረዳው ግለሰብም በጥበብና በብልሃት የመጡትን የአሸባሪውን ቡድን ታጣቂዎች አዘናጋቸው።

ሊያጠቁትና ሊዘርፉት እንደመጡ የተረዳው ይህ ግለሰብ ያለውን መሣሪያ በመጠቀም በቤቱ የተሰበሰቡትን 11 የአሸባሪውን ትህነግ ታጣቂዎች እንዳልሆኑ በማድረግ ጀግንነቱን አሳይቷል።

አሁን ላይም ይህ ጀግና ቀሪ የአሸባሪውን ቡድን አባላትን እያሳደደ ይገኛል።

ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ክብርንና ማንነትን ማስጠበቅ የሚቻለው ይህንን አይነት ቆራጥነት በጠላት በመፈጸም ነው።

የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ ቀለመወርቅ ምህረቴ እንደዚህ አይነት ቁርጠኝነት ካለ ጠላት በየትኛውም አካባቢ ለእንቅስቃሴ እንዳይመቸው ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡

Previous article❝አሸባሪውና ወራሪው ትህነግ ወረራ በፈፀመባቸው ሁሉም አካባቢዎች የፀጥታ ኃይላችንና ሕዝባችን በተቀናጀ ሁኔታ እየመከቱት ይገኛል❞ የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት
Next article“የተፈረሙ ስምምነቶች የሀገራቱን ግንኙነት መጠናከር ያመላክታሉ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ